
By Patriotic Ginbot7,
AS YOU have already learnt, our struggle against the minority TPLF-led regime in Ethiopia has reached a crucial milestone at which our comrades have begun paying the ultimate sacrifice.
Armed struggle has never been our primary choice of the struggle. However, after closing all avenues of peaceful resistance, the regime has left us with the only options of either to remain enslaved losing all our civil liberties and freedom on our home land or to fight back and regain our democratic rights.
Today, Chairman of our struggle and one time democratically elected mayor of the capital Addis Ababa, Dr. Berhanu Nega, has finally joined his comrades in arms on the ground so as to lead the struggle of freeing the Ethiopian people from the clutches of the TPLF apartheid regime.
As we have confidence in the victory of good over evil, we have no doubt that Dr. Berhanu Nega and other leaders of our organization will effectively lead our struggle to freedom, justice and democracy!
ከቃሊቲ እስር ቤት ከተፈታ በሁዋላ ወደ አሜሪካ በመመለስ በተማረበት ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር በመሆን ሲያገለግል ከቆየ በሁዋላ ከጥቂት ወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ ተሰጥቶት በበክኔል ዩኒቨርሲቲ በስራ ላይ ቆይቷል። ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማእረግ እንደ ተሰጠው የሰሙ ጋዜጠኞች ደስታቸውን ገልጸው ዜናውን ለመዘገብ ሲጠይቁት “ፕሮፌሰርነት ተራ ነገር ነው። የእኔ ስራ ማስተማር ሳይሆን በአስከፊ ጭቆና እና ዘረኝነት ስር ወድቆ የሚማቅቀውን ህዝቤን ነጻ ማውጣት ነው” ሲል ጋዜጠኞቹ ተደምመው ነበር።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚህ በአሜሪካን ሃገር የፕሮፌሰርነት ህይወቱን ትቶ በረሃ የወረደው ምንም ጎሎበት አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንባና መከራ፣ ህመምና ሰቆቃ እንቅልፍ ስለነሳው ብቻ ነው ዛሬ ያፈራውን ሃብትና ንብረት ሽጦ ህዝቡን ነጻ ሊያውጣ ከፊት ሆኖ ሊመራ ከድካሙ አረፍ ብሎ በመኖሪያ እድሜው በረሃ የወረደው።
የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ግንባር መሄድ ያለው ትልቅ እንድምታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። የቆረጠ ለውጥ ማምጣቱ አይቀርም። ፕሮፌሰር ብርሃኑ የሚሞላው አንድ ታላቅ ክፍተት ህዝባችን የሚከተለው መሪ በአስተማማኝ ሁኔታ ማግኘቱ ነው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በተግባር እና በእሳት የሚፈተን መሪ ለመሆን ወስነህ ሁሉን ትተህ ወደ ግንባር መውረድህ የሚያመጣው ለውጥ ቀላል እንዳልሆነ እኛም ብቻ ሳንሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶችም ጠንቅቀው ያውቃሉ።
ታላቅ መሪ በተግባር ይፈተናል። እስከ መጨረሻው የነጻነት መዳረሻ ከጎንህ እንሰለፋለን። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! (ከ ኣበበ ገላው)