Mengistu Hailemariam Reportedly to Move to South Sudan as Guest of Honor

News
Ethiopia’s former dictator and Butcher Mengistu Hailemariam

The Reporter,

Former Ethiopian president, Mengistu Hailemariam, is reportdely planning to move to his new relocation – South Sudan, according to Reporter news paper.

The government of South Sudan has furnished him with a modern building for the former president who is currently living in Zimbawe, Reporter added quoting informed sources.

Southern Sudanese are apparently grateful to Mengistu Hailemariam for providing them with invaluable assistance during their liberation struggle against the Khartoum regime.

The News in Amharic language (you may need Geez fonts to read it):

ደቡብ ሱዳን ለመንግሥቱ ኃይለማርያም መኖርያ ቤት ሠራች

 ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ነፃነቱን ያወጀው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሌተና ኰሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቤት ሠርቶ ያጠናቀቀ መሆኑን የደቡብ ሱዳን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ከምንጮቻችን ለመረዳት እንደቻልነው፣ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለሌተና ኮሎኔል መንግሥቱና ቤተሰቦቻቸው መኖርያ የሚሆን ዘመናዊ ቤት እንዲሠራ ያደረገው፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በነፃነት ትግሉ ወቅት ለደቡብ ሱዳን የሰጡትን ድጋፍ በማስታወስ ነው፡፡ 

‹‹ኮሎኔል መንግሥቱና መንግሥታቸው በነፃነት ትግሉ ወቅት ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ የሰጡት ድጋፍ መቼም የሚረሳ አይደለም፤›› ያሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ቢሮ አንድ የሥራ ኃላፊ፣ መንግሥታቸው ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ የዋሉትን ውለታ ትኩረት ውስጥ በማስገባት ዘመናዊ መኖርያ ቤት ሠርቶ ያጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶበት የተሠራው ይኼው የሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ቤት በፀጥታ ሰዎች ጥብቅ ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን የገለጹት ምንጮቻችን፣ ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ የደቡብ ሱዳን መንግሥትን ግብዣ ተቀብለው በቅርቡ ወደ ጁባ ያመራሉ የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዘመነ ደርግ ለደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ግንባር ሠራዊት ሙሉ ድጋፍ መስጠቷና ለመሪው ዶክተር ጆን ጋራንግ በመዲናዋ አዲስ አበባ መኖርያ ማዘጋጀቷ ይታወሳል፡፡ (Source)

‹‹ለመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ቤት አልሠራንም›› የደቡብ ሱዳን መንግሥት

‹‹ደቡብ ሱዳን ለሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ቤት ሠራች›› ተብሎ ባለፈው ረቡዕ የደቡብ ሱዳን ምንጮችን ዋቢ አድርጎ የተዘገበው ዜና ትክክል አለመሆኑን፣ በኢትዮጵያ የሱዳን ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

የደቡብ ሱዳን ኢምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚስተር ዴቪድ ዳንግ ኮንግ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሱዳን መንግሥት ለሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ቤት መሥራት ይቅርና ምንም ዓይነት ግንኙነት አድርጐ አያውቅም፡፡ 

የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ከፍተኛ ድጋፍ ሲደረግለት የነበረው በኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን ያስታወሱት ምክትል አምባሳደሩ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ያደረጉት ውለታ ለኮሎኔል መንግሥቱ ተደርጐ ሊወሰድ እንደማይገባ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለቀድሞው ፕሬዚዳነት መኖርያ ቤት ሠርቷል ተብሎ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንታዊ ቢሮ ምንጮች የተገኘው ዘገባ ሐሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

አዲስ አበባ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን መንግሥት አገናኝ ቢሮ ለሪፖርተር ጋዜጣ የላከው የማስተባበያ ደብዳቤም እንዲህ ይላል፡፡ “የደቡብ ሱዳን መንግሥት አገናኝ ቢሮ ለሪፖርተር ጋዜጣ ያለውን ምስጋና እየገለጸ፣ ሐምሌ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ቤት ሠራች የሚል ዘገባ ይዞ የወጣውን ሪፖርተር ጋዜጣ ያነበብን መሆናችንን በአክብሮት ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ በመሆኑም ዜናው ሙሉ በሙሉ እውነት ባለመሆኑ በጋዜጣው ላይ ማስተካከያ እንድታወጡልን ቢሮአችን በትህትና ይጠይቃል፡፡ የደቡብ ሱዳን መንግሥት አገናኝ ቢሮም ይህንን አጋጣሚ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ እንደሚጠቀምበት ያረጋግጣል፤” ብሏል፡፡  (Source)