
By TesfaNews,
The press and media in Ethiopia has been shocked, surprised and even angered by the invitation and the extremely warm welcome that was extended by President Museveni of Uganda to President Isaias Afwerki of Eritrea, for his three days state visit to the country.
Their frustration begins the day they heard Uganda declare Eritrea as “one of the strategically vital countries to the stability of the region, especially in the Horn of Africa and the wider global agenda.” However, what they have failed to understand is, in politics, there are no permanent friends but permanent interest. Uganda is after its interest and so does Eritrea and the rest of the world.
For now, we will present the articles posted on two major Ethiopian newspapers, Addis Fortune and The Reporter (Amharic version) respectively, for you to judge for yourself how they find it difficult to swallow the sudden change of events and diplomatic prostitution.

Redemption Mission?
Much of the excitement was caused with Eritrea currently being in the limelight for the last couple of months over alleged support for extremists groups in East Africa, and in the past both Kampala and Asmara had traded accusations over Eritrea’s support for al Shabaab.
At the press conference held on August 18, 2011, and waiting for their turn to throw their questions where the war torn stateless country of Somalia was the main agenda of the press conference, Isaias and Museveni told the media that Eritrea is not supporting al Shabaab, a militant Islamic group that controlled most of Southern Somalia.
The group is also accused of having ties to Al-Qaeda and masterminded the Kampala bombing during the 2010 World Cup final that killed 79 people, including one Ethiopian and six Eritrean.
Al Shabaab is fighting to overthrow the Transitional Federal Government of Somalia (TFG), which is backed by Ethiopia, the African Union and the international community.
“Al Shabaab is not supported by Eritrea. That is what he told me,” President Museveni told the media referring to his closed meeting with President Isaias.
Such a statement to come from a leader of the country, which has peacekeeping troops conducting deadly operations with al Shabaab militia, was unexpected.
Two weeks prior to the two presidents’ meeting, 25 Ugandan soldiers were killed in Mogadishu during fighting with al Shabaab militia, according to Ugandan media. The bodies of the three soldiers also dragged through Mogadishu streets.
Uganda and Burundi are the only two countries that have sent their 9,000 troops for the African Union’s peace keeping mission in Somalia known as AMISOM.
When asked whether President Museveni accepted assurances from Isaias that Eritrea did not support al Shabaab Museveni responded: “I accept it because he told me. He is an honourable comrade.”
“He [Isaias] is not somebody who walked out of the slums,” President Museveni replied while Isaias laughing on the response. However, Museveni tried to clarify that the Kampala twin blasts was masterminded by al Shabaab.
“The bombing was done by al Shabaab but al Shabaab is not supported by Eritrea,” he said.
The presidents’ stand is in total contrast with the report of the UN Monitoring Group report released in late July 2011. The report alleged that Eritrea was bankrolling al Shabaab through its embassy in Kenya. It is also echoed by the Ethiopian government’s claims that Eritrea was behind a plot to attack the African Union summit held in Addis Ababa in January 2011.
According to the report, the plan was to attack the AU headquarters with a car bomb when African leaders took breaks. The plan also included on an attack in the area between the Prime Minister’s Office and Sheraton Hotel, where most heads of state stay during AU summits.
The report alleged that blowing up Merkato, Africa’s largest market, and “killing many people” was also part of the plan. President Isaias ridiculed the Monitoring Group’s claims when journalists asked questions regarding the report. He appeared combative in his responses.
“It is very sad that all these fabrications have made their way into the minds of many, including the media,” President Isaias said. “I would urge everyone to revisit all that disinformation that comes from here and there.”
The Eritrean President and his government officially has repeatedly rejected claims of the UN monitoring group, however, the 15-member UN Security Council is assessing the proposal of another sanction on Eritrea based on the findings of the report. Eritrea’s neighbours, Ethiopia and Djibouti mounted their pressure for the endorsement of the sanction.
The two countries pushed the sanction through the East African regional bloc, the Inter Governmental Intergovernmental Authority on Development (IGAD). IGAD called for sanctions against Eritrea’s mining interests and banned a tax on remittances sent back by Eritreans in the Diaspora. The bloc’s call later was supported by the African Union.
“These new sanctions may be difficult to carry out but there is certainly agreement on the Security Council now that something has to be done about Eritrea,” a Western diplomat at the UN told AFP news agency.
President Isaias refused to accept that there is ongoing pressure on his country.
“Those who perceive pressure on Eritrea are wishful thinkers. The dream of something that does not exist. Pressure cannot be exerted on Eritrea on fabricated lies,” he told the media.
“This is sickness on my opinion,” he said.
The country already tastes the damage of pressures and its consequences. In 2009, the UN Security Council passed sanctions against Eritrea over its support for insurgents in Somalia.
The sanction, which is first cooked by IGAD, imposed an arms embargo, travel restrictions and asset freeze on top Eritrean political and military leaders. Ironically, Uganda, is the one who floored the sanction proposal to Security Council.
The recent move of Eritrea to rejoin IGAD and Isaias’ visit to Uganda is taken as diplomatic effort to ease the pressure on the country and returning to the international community from isolation. “Eritrea does not have friends. [Isaias] could be attempting to mend fences,” Dr Philip Kasaija, a lecturer of International Law University at Makerere University, told the Ugandan bi-weekly newspaper, the Observer.
Isaias was dismissing the idea of making friends and asking friends for some help. “I did not ask President Museveni for any help on that,” Isaias said with laugh. In response, Museveni backed Isaias. “He did not ask me any help,” he agreed.
The two leaders showed almost no disagreement during the press conference. Isaias referred to Museveni as “brother” and Museveni used the word “comrade”, as a nod to their shared past as rebel fighters. They both still seem fond of their old days of fighting. (Source)

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ – የመንታ እናት ተንጋላ ትሞት!?
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰሞኑን የኡጋንዳ የሦስት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅት ቆይታቸውን በተመለከተ ከፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን በሰጡት መግለጫ፣ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ቀዳሚው ጥያቄ ከአልሸባብ ጋር ያላቸውን ቁርኝት በተመለከተ ማብራርያ እንዲሰጡ ነበር፡፡
ፕሬዚዳንቱም ‹‹The issue here is not Alshabab›› (ጉዳዩ የአልሸባብ አይደለም) ማለታቸውን ሮይተርስን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና የኡጋንዳ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት በኡጋንዳ መዲና በካምፓላ አልሸባብ ኃላፊነት የወሰደበትን የሽብር ጥቃት የሚያስታውሱት የኡጋንዳ ጋዜጠኞች ግን፣ የቡድኑ የጀርባ አጥንት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመራው የአስመራው መንግሥት መሆኑን ስለሚገነዘቡ፣ ደጋግመው ጥያቄውን አነሱባቸው፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ደግሞ በጥያቄዎቹ መደጋገም አልተደሰቱም፡፡ የጋዜጠኞቹ ጥያቄ መሠረት ያደረገውም በካምፓላ ሳይቀር አሰቃቂ ግፍ የፈጸመው አሸባሪ ቡድን የሚደገፈው በኤርትራ መንግሥት መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሰሞኑን ይፋ መደረጉን ነው፡፡ ይህንን ልብ ያሉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግሥታቸው ከአልሸባብ ጋር ስላለው ትስስር አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹አሁን ግን ጉዳዩ የአልሸባብ አይደለም›› በማለት ምላሻቸውን የቀጠሉት እንደ ወትሮው ሁሉ በሪፖርቱ ውስጥ የቀረቡትን ማስረጃዎች ሽምጥጥ አድርገው በመካድ ነው፡፡ ‹‹እየቀረቡ ያሉት ውንጀላዎች በመላምቶች፣ በይሆናልና በግምቶች ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤›› በማለት የተመድ አጣሪ ቡድን ሪፖርትን አጣጥለዋል፡፡ ‹‹እኔ አልሸባብን አልደገፍኩም፡፡ በመጥፎ ተግባር ላይ ተሰማርቼም አላውቅም፡፡ የእኔ ፍላጎት ነፃ የወጣችና የተዋሀደች ሶማሊያን ማየት ነው፤›› ማለታቸውን ቀጠሉበት፡፡
በአንድ ራስ ሁለት ምላስ
ተመድ ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው ሪፖርቱ የኤርትራን መንግሥት የሽብር ተግባር ተባባሪና ደጋፊ በማለት ወንጅሏል፡፡ ተመድን እዚህ ውሳኔ ላይ ያደረሰው ወደ ሶማሊያ፣ ኤርትራና ኢትዮጵያ በማሰማራት በአጣሪ ቡድኑ አማካይነት የተገኘን ታማኝ ማስረጃ መሠረት አድርጎ ሲሆን፣ የቀረበው ሪፖርትም ሰፊና 470 ገጾችን የሚሸፍን ነው፡፡ በዚሁ ሪፖርቱ ኤርትራ በሶማሊያ ለሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛው አልሸባብ ሙሉ ወታደራዊ ትጥቅ፣ ሥልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እያደረገች መሆኗን አረጋግጧል፡፡ ከዚያም አልፎ በጥር 2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ ወቅት፣ የኤርትራ መንግሥት ‹‹አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ›› የማድረግ የከሸፉ ፍንዳታዎችን ለማድረስ መሞከሩ በአጣሪ ቡድኑ ተደርሶበታል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች በተለይ ደግሞ ጂቡቲንና አዲሷን ደቡብ ሱዳንን ለማተራመስ እየተንቀሳቀሰ መሆኑም እንዲሁ በሪፖርቱ ተረጋግጧል፡፡
ይህንን ተከትሎ በተለይ በአሜሪካ ውትወታ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየተንቀሰቀሰ ነው፡፡ 15 አባላት ያሉት ይኼው የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዕርምጃውን ለመውሰድ ከወዲሁ እንዲነጋገርበት ግፊት እየተደረገ ነው፡፡ በተመድ የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሱዛን ራይስ በኤርትራ ላይ ጠንከር ያለ ማዕቀብ እንዲጣል የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀድሞውና ተግባራዊነቱም እስከዚህም በሆነው ማዕቀብ ብዙም አልተቸገረም የሚባለው የአስመራ መንግሥት፣ ከጎረቤቶቹ በተጨማሪ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ተገልሎ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን የአቋም ለውጥ ማድረጉን አመላካች ዕርምጃዎች እየወሰደ ይመስላል፡፡ ተመድ ተጨማሪውን ማዕቀብ ከመጣሉና የባሰ ውጥረት ከመፈጠሩ በፊት መለሳለስ እያሳየ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ካሁን በፊት ይታዩበት የነበሩ አወዛጋቢ ባህርያቱ መቀየር የጀመሩት፡፡
ተመድ የኤርትራን ለአካባቢው ስጋት መሆን የሚያሳየውን ጠንካራ ሪፖርት ባወጣ ማግስት፣ ከአስመራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥርያ ቤት የተላከለትን ማመልከቻ የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ተቀብሏል፡፡ ‹‹ወደ ኢጋድ አባልነት ለመመለስ እንፈልጋለን፤›› የሚለው የኤርትራ ጥያቄ ግን እስካሁን ምላሽ አላገኘም፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 በናይሮቢ ኢጋድ ባካሄደው ስብሰባ ‹‹የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ይግቡ አይግቡ›› በሚለው ክርክር ላይ ነበር ተቀናቃኙ የኤርትራ መንግሥት ‹‹ይህንን የምትወስኑ ከሆነ ራሴን ከኢጋድ አግልያለሁ›› ያለው፡፡ አሁን ግን በተመድ አማካይነት በዚሁ መንግሥት ላይ ተጨማሪ የማዕቀብ ዕርምጃ እንዲወሰድ የውሳኔ ሐሳብ ያቀረበው ኢጋድ ነው፡፡ የሽብር ድርጊቱን የሚገልጽ በቂና አስተማማኝ ማስረጃ በማቅረብ፡፡
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ የኢሳያስ መንግሥት ወደ ኢጋድ ለመመለስ ሐሳብ ያቀረበው በተመድ ‹‹ከነገ ዛሬ›› ይወሰዳል የተባለውን ጠንካራ ማዕቀብ በመስጋት እንጂ፣ መሠረታዊ የአቋም ለውጥ በማድረግ አይደለም፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር አቶ አብዲዋሳ አብዱላሂ፣ ‹‹አሁን ባለንበት ዓለም ተነጥሎ መኖር አይቻልም፡፡ እንኳን ትናንሽ አገሮች እንደ አሜሪካ የመሳሰሉ ኃያላን አገሮችም የሚችሉት አይደለም፡፡ እውነት የኤርትራ መንግሥት ይህንን ተገንዝቦ ሰላም ለመፍጠር ፈልጎ ከሆነ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ጊዜያዊ ታክቲክ ከሆነ ግን . . . ›› ብለዋል፡፡
ወታደሮችዋን በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪነት በሶማሊያ ያሰማራችው ኡጋንዳ አሁን በፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቀዳሚነት ለጉብኝት የተመረጠችውም ለዚሁ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሱት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ 79 የሚሆኑ ዜጎቿን ያጣችበትን የካምፓላ የአልሸባብ የሽብር ጥቃት አልነበርንበትም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ይመስላል፡፡ አቶ አብዲዋሳም ይህንን ሐሳብ ይጋራሉ፡፡ የተመድ ተጨማሪ ማዕቀብ ከመጣሉ በፊት ራስን ከአልሻባብ የማራቅ የተንኮል ስትራቴጂ የሚሉትም አሉ፡፡
ቀደም ሲል በተሰነዘሩባቸው ውንጀላዎች ለአልሸባብ የነበራቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ያልተበገሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቡድኑን፣ ‹‹የሶማሊያ ነፃ አውጪ›› በማለት ያንቆለጳጵሱት እንደነበር ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ በወቅቱ ‹‹ታጋዮች›› በማለት በተናገሩበት ልሳን በአሁኑ ጊዜ ይህንን ቃላቸውን አጥፈው የአልሸባብን አባላት ‹‹አሸባሪዎች›› ብለዋቸዋል፡፡ ‹‹አልሸባብ የሶማሊያን አንድነት ለመበታተን የሚቋምጡ አባላት ስብስብ ነው፡፡ በሶማሊያ ያለው ሁኔታ እየከበደ እንዲሄድ አስተዋጽኦ አድርጓል፤›› ብለዋል፡፡
የኡጋንዳው ጉብኝታቸው ዘላቂ ፖለቲካዊ አንድምታው በጊዜው የሚታይ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንቱ ለጊዜው ተስፋ የሰነቁበት ይመስላል፡፡ የአፍሪካ ውህደትን ጨምሮ በበርካታ ክልላዊና አኅጉራዊ ጉዳዮች ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ይስማማሉ ተብሎ የሚታመንባቸው ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ፣ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጉብኝት የሰጡት የክብር አቀባበል፣ በተለይ ደግሞ ከምክክራቸው በኋላ ባሰሙት ንግግራቸው የነበራቸው አወንታዊ አመለካከት ግራ መጋባትን ፈጥሯል፡፡ በጋራ መግለጫው ወቅት ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ፣ ‹‹እዚሁ ለተፈጸሙት የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂው አልሸባብ ነው፡፡ ዋናው ቁምነገር ግን አልሸባብ በኤርትራ የሚደገፍ አለመሆኑ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ያሉኝም ይህንን ነው፡፡ እኔም አምኜ ተቀብያቸዋለሁኝ፡፡ ምክንያቱም ከየትም ተራ ቦታ የመጡ ሰው ሳይሆኑ የተከበሩ ጓድ ናቸው፤›› በማለት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሐሳብ ልባቸው መሸነፉን አምነዋል፡፡
የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ ሆኖባቸው ይሁን ወይም ከልባቸው አምነውበት ሙሴቬኒ እንዲህ ይበሉ እንጂ፣ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማሳየት የሞከሩት በዓለም የተገለሉትንና አካባቢውን በማተራመስ የሚታወቁትን ኢሳያስን ለማግባባት ነበር ይላሉ፡፡ በአልሸባብ መዳከም ተስፋ የቆረጡና ቡድኑን በመደገፋቸው ምክንያት የሚከተላቸው ጠንካራ ማዕቀብ ላሰጋቸው ኢሳያስም፣ የእንዲህ ዓይነቱን መሪ ድጋፍ ማግኘት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ቀልብ ለማስቀየስ ቀላል ዘዴ አይደለም፡፡
የፖለቲካ ተንታኙ አቶ አብዲዋሳ፣ ኢሳያስ ብቸኝነት የማያዋጣ መሆኑን የሚገነዘቡ ይመስለኛል፡፡ ማዕቀቡ በበዛ ቁጥር የኤርትራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን አመራሩን ጭምር ነው ከአካባቢውም ከዓለምም የሚነጥለው፡፡ ኢሳያስ ይኼ ደግሞ ከተሳካላቸው በአልሸባብ ተጠቂ ከሆነችው ኡጋንዳ በኩል ያለው ግፊት ይቀንስላቸዋል፡፡ በእርግጥ ከገፉበት ደግሞ መልካም ጉርብትና መጀመር ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው፤›› ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
‹‹የኢትዮጵያ የሻጥር ዘመቻ?››
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተመድ የቀረበባቸውን ዝርዝር ሪፖርት ካለመቀበላቸውም በላይ ሌላ ትርጉም ሰጥተውታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያስፈጽሙት የነበረውና የከሸፈው የሽብር ሙከራ በተመድ ተቀባይነት ማግኘቱ እጅግ ያስቆጣቸው ኢሳያስ፣ እየተደረገ ያለው በሙሉ ‹‹የኢትዮጵያ የሻጥር ዘመቻ›› ነው ብለውታል፡፡ ‹‹አሰልቺ›› ያሉትን ይህንን የተመድ ሪፖርት ክስ ሲያስተባብሉ፣ ‹‹በታሪካችን የመጥለፍ፣ የማገትና የማፈንዳት ባህል የለንም፤ የተካሄደብን የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው፤ የታሪካችን አካልም አይደለም፤ አሁን እነዚያና እነዚህን የውሸት ክምሮች አሰባስቦ ማሰራጨትና በእኛ ላይ ጥርጣሬዎችን መፍጠር የሚሠራ አይሆንም፤›› ብለዋል፡፡
እንደ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አባባል ይኼ ሪፖርት የተቀነባበረው በኢትዮጵያ መንግሥት ሴራ ሲሆን፣ ይህም ሴራ ኤርትራ በቅርቡ የምታገኘውን የወርቅ ሽያጭና የዳያስፖራ ገቢን ለማስቀረት ያለመ ነው፡፡ በዚህም በአስመራ የመንግሥት ለውጥ ለማድረግና የባህር ወደብን መልሶ የማግኘት ዕቅዱን ለማሳካት የኢትዮጵያ መንግሥት ማሰቡን ወንጅለዋል፡፡
‹‹የሚያሳዝነው ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው የሻጥር ዘመቻ ነው፡፡ በኤርትራ ላይ አስከፊ ችግር የሚያስከትል የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል ኤርትራ የአፍሪካ ቀንድን እያተራመሰች ነው የሚለውን እንደ ሽፋን እየተጠቀመችበት ነው፤›› ብለዋል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፡፡ አቶ አብዲዋሳ ግን የኤርትራ የሽብር እንቅስቃሴ ከስም ማጥፋት ጋር የሚያያዝ አይደለም ይላሉ፡፡ ‹‹ምንም ችግር ከሌለብህ ጎረቤቶችህ በሙሉ ቅሬታ ሊያቀርቡብህ አይችሉም፡፡ ዓለምና የሶማሊያ ሕዝብ ከጠላው አልሸባብ ጋርስ መጠጋት ለምን አስፈለገ?›› ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡
በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ ልዑክ ቃል አቀባይ አቶ ዳንኤል ይልማ ወርቄ በበኩላቸው፣ ይኼ የኤርትራ ‹‹የማስቀየስ ስልት›› ነው ያሉት፡፡ ‹‹የተመድ አጣሪዎች ኤርትራ ከማተራመስ ድርጊቷ አለመቆጠቧን አረጋግጠዋል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ላይ እየቀረበ ያለው ክስ ሆን ተብሎ የታሪኩን አቅጣጫ ለማስቀየስ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በኤርትራ ላይ እየታሰበ ያለው ጠንካራ ማዕቀብ ‹‹ኢኮኖሚንም›› የሚያጠቃልል ሲሆን፣ በቅርቡ ኤርትራ ከፍተኛ ገቢ ያስገኘላትን የወርቅ ኤክስፖርት ገቢ ያስከለክላል፡፡ ኢኮኖሚዋ በአብዛኛው የተመሠረተበትን በውጭ ከሚኖሩ ዜጎች የሚገኘው ገቢ ላይም ጭምር ያነጣጠረ በመሆኑ ለኤርትራ መንግሥት የራስ ምታት ሆኗል፡፡
‹‹የውሸት ሪፖርቶች›› ወይስ . . .?
የኤርትራ መንግሥት ዓለም አቀፍ ውግዘት እየወረደበት ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለውን ‹‹ደካማውን›› የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ለመጣል የሚንቀሳቀሰውንና ከአልቃይዳ ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለውን አልሸባብ ሙሉ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተረጋግጧል፡፡ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ፈንጂዎችን በማፈንዳት ለመበጥበጥ ሙከራ ማድረጉም እንዲሁ፡፡
ኢጋድ፣ የአፍሪካ ኅብረትና ተመድ የኤርትራ መንግሥትን ሲያወግዙ የመጀመርያቸው አልነበረም፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት በሶማሊያ የፈጸመውን ሕገወጥ ጣልቃ ገብነቱንም አውግዘዋል፡፡ ሱዳንን፣ የመንንና ኢትዮጵያን በመውረርና በመተንኮስም በየጊዜው ግጭት መፍጠሩን አረጋግጠዋል፡፡ በቅርቡም ጂቡቲንና ሶማሊያን በማሸበር በባለሥልጣናቱ የመንቀሳቀስ መብትና በጦር መሣርያ ዝውውር ላይ ማዕቀብ ተጥሎበት ነበር፡፡ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመራው መንግሥት ግን እንደዚህ ዓይነት ሪፖርቶችንና ወቀሳዎችን ‹‹መሠረት የሌላቸው›› በማለት ከማብጠልጠል ውጪ አንድም መሻሻል ሲያሳይ አይስተዋልም፡፡ በአገር ውስጥ ለሚነሱበት የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በአካባቢው ለሚፈጸሙ የትንኮሳና የማተራመስ እንቅስቃሴ ወቀሳዎች ሁሌም በኤርትራ በኩል ሁለት ምላሾች ይሰጣሉ፡፡ በአንድ በኩል የድንበር ኮሚሽኑ የፈረደለትን ባድሜን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያን ግዛቶች ሳልረከብ እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎችን አላስተናግድም የሚል ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲህ ዓይነት ትችቶችን የሚያወጡ ምዕራባውያን በተለይ ደግሞ የአሜሪካ መንግሥትና እዚያው የከተሙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን በጠላትነት ይፈርጃል፡፡ ‹‹በአፍሪካ ቀንድ ለሚያራምዱት ፖለቲካ ታዛዦች ባለመሆናችን ነው፤›› በሚል ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ እንድትቀበል አላስገደደም የሚልም ሌላ ሰበብ ይመዛል፡፡
በቅርቡ በምሥራቅ አፍሪካ የተከሰተውን ድርቅና ረሃብ ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት ዜጎቹ እየተራቡ ለዓለም ማሳወቅ አልፈገም ተብሎ ይከሰሳል፡፡ የረድኤት ድርጅቶችና የተመድ የተለያዩ አካላት በኤርትራ አስቸኳይ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች አሉ ሲሉ ይወቅሳሉ፡፡ የኤርትራ መንግሥት አሁንም ከማስተባበል ውጪ ሌላ ምላሽ የለውም፡፡
በዚህ ዓይነቱ አጣብቂኝ ውስጥ ያለችው ኤርትራ ሌላ ዙር ጠንካራ ማዕቀብ ሲጋረጥባት የኤርትራ መንግሥት በዲፕሎማሲው መስክ መንቀሳቀስ ቢጀምርም፣ ይሳካለታል ብለው የሚጠብቁ ወገኖች ካሉ ተሳስተዋል የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ፡፡ አሜሪካ በዓለም ላይ በቁጥር አንድነት የፈረጀችውን የአልቃይዳ ወዳጅ ጽንፈኛውን አልሸባብ ሲደግፍ የነበረው የኤርትራ መንግሥት ተገቢውን የማዕቀብ ቅጣት ሳያገኝ እንቅልፍ አይኖራትም እየተባለ ነው፡፡
ይህ ዓይነቱ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ያለው የኤርትራ መንግሥት ከወታደራዊና ከብጥበጣ ተግባሩ ለዘብ ብሎ መታየት የፈለገው፣ ሲመቸው የተለመደ ተግባሩን ለማስቀጠል አልሆን ሲለው ደግሞ ሰላማዊ መንገድ እከተላለሁ በማለት ሁለቱንም ማጣቀስ ስለፈለገ ነው የሚሉ አሉ፡፡ “የመንታ እናት ተንጋላ ትሞት” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡ (Source)